ኤሪክ ብሌይር ይሰኛል በብዕር ስሙ ደግሞ ጆርጅ ኦርዌል ፤ ካሉት በርካታ መፅሐፍት ውስጥ በዝናው ስለናኘው 'Animal Farm' እንዲህ እንጫወት።
መፅሐፉ በ1917 የተቀሰቀሰው የሩሲያ አብዮት ሩሲያውያንን ወደምጨቁን አምባገነናዊ መንግስት እንዴት እንደተቀየረ የምታርክ ተምሳሌታዊ ልቦለድ ነው።
የታሪኩን ጥንስስ በሀገረ እንግሊዝ ባለ የMr.Jones 'manor Farm' በመተረክ ይጀምራል። Mr.Jones ለእንስሳቱ ግድየለሽ ፣ ሲሻው የሚቀጣ ጨካኝ ፣ ሲሻው የምሸልም ርሁሩህ የእርሻው ጌታ ነበር። ⁵[በእርግጠኛ ባለመሆን መርህ] እንስሳቱን ልያስተዳድር የሚሞክር አይነት የእርሻ ባለቤት!
ከእለታት አንድ ቀን 'old major' የተሰኘው አሳማ ከእንስሳቱ ጋ መከረ። ስለምደርስባቸውም በደል 'Beast of England' የተሰኘ የአብዮት ዜማ ደረሰ። መተዳደሪያ ማኒፌስቷቸውንም በእንስሳቱ እኩልነት ፣ በሰው ልጅ ጠላትነት እና እንስሳቱ የተሻለ ሕይወት እንደሚያሻቸው በሚያትት ውቅር መርሆዎች 'Animalism' ብሎ ሰየመ።
'manor farm' ሩሲያ ነበረች። ከአብዮቱ በፊት ልክ እንደ Mr.Jones በሚወዥቅ ባህሪ የሚያስተዳድረት ኒኮላስ ሁለተኛ የተሰኘ ንጉሥ የነበራት ሀገር ። ካርል ማክስ የሰራተኛውን መደብ መጨቆን ነፃ የሚያወጣ የኮሚኒዝም ማኒፌስቶን አስተዋወቀ። ሩሲያም ነፃነትን ፍለጋ በተነሳ አብዮት ጋለች።
ልቦለዱ በ'snowball' እና 'Napoleon' በተሰኙ አሳማዎች አመራር አብዮቱ እንደቀጠለ ይተርካል።
snowball ስለእንስሳቱ ሕይወት መሻሻል የምታትር ሀሳባዊ መሪ ሲሆን ፩.አሁናዊ አላማቸውንና የወደፊት ህልማቸውን የሰነደ ባንዲራ አዘጋጀ ። "The flag was green, Snowball explained, to represent the green fields of England, while the hoof and horn signified the future Republic of the Animals which would arise when the human race had been finally overthrown."
፪.ቀለም ጨበጠ የእርሻውንም ስም ANIMAL FARM ብሎ ዳግም ሰየመው "Then Snowball (for it was Snowball who was best at writing) took a brush between the two knuckles of his trotter, painted out MANOR FARM from the top bar of the gate and in its place painted ANIMAL FARM."
፫.የAnimalism ማኒፌስቶን 'በሰባቱ ትዕዛዛት' ፃፈ።
THE SEVEN COMMANDMENTS
1. Whatever goes upon two legs is an enemy.
2. Whatever goes upon four legs, or has wings, is a friend.
3. No animal shall wear clothes.
4. No animal shall sleep in a bed.
5. No animal shall drink alcohol.
6. No animal shall kill any other animal.
7. All animals are equal.
'Napoleon' ግን ጨካኝ ፣ መሰሪና ና አምባገነን መሪ ነበረ። ልክ አሜሪካዊው የመድረክ ቧልተኛ የአሜሪካ ፖለቲከኞችን ስወርፍ ⁶"why they call it American dream,to belive them you have to asleep" ያለው የቀልድ አልጎሪ በልኩ የተሰፋለት ገፀባህሪይ ! በእርሻው ውስጥ ጠባቂ ውሾችን በማሰልጠን ግላዊ ሃይሉን አደረጀ፣ 'squealer'ን ለፕሮፓጋንዳው በመጠቀም በእንስሳቱ ዘንድ እምነት አሳደረ ! ከዚያም snowballን ከእርሻው በማሳደድ አባረረው።
snowball በሩሲያ አብዮት ውስጥ የ "October Revolution" የመራው የፓሊስ ነዳፊው የሊዮን ትሮቶስኪ ተምሳሌት ነበረ ። የሩሲያንም ስም ወደ USSR ቀይሯል። Napoleon ደግሞ ጨካኙን ስታሊን ሲሆን ያሰለጠናቸው ውሾች ደግሞ የስለላውን ዋልታ KGB ተምሳሌት ነበሩ። ልክ እንደ Snowball ትሮቶስኪ በስታሊን ከሀገሩ ሩሲያ ተባሯል።
_
Napoleon የአምባገነንነቱን ደርዝ አሰፋ። የታታሪዎቹ እንስሳት እምነት "Napoleon is always right, I must work harder-'Boxer' " ፣ የማያሰላስሉትን በቀላሉ ማሞኘት መቻሉ ፣ በአብዮቱ ውስጥ የራሳቸውን ሕልም የሚያልሙ እንስሳት መኖራቸው (አለ አይደል እንደግራጫ ቃጭሎቹ መዝገቡ ኢምፔሪያሊዝም ይውደም ሲሉ ሰምቶ ልሙጥ ሽሮ ይውደም እንዳለው😂)The stupidest questions of all were asked by Mollie, the white mare. The very first question she asked Snowball was: “Will there still be sugar after the Rebellion? “ እነኚህ ምክንያቶች ለሚቀይራቸው ሕጎች ⁷የቅቡልነትን ሕግን ለማስረፅ እንዲቻለው አቅም ሰጠው ።
በእርሻው ላይ ሰባቱ ትዕዛዛት እንዲህ ተለውጠዋል ፤ ◉“No animal shall sleep in a bed” to “No animal shall sleep in a bed with sheets” አልጋ አንጥፈው እየተኘ ፤ ◉"No animal shall drink alcohol" to "No animal shall drink alcohol to excess" በውስኪ ስካር እየተዘፈቀ ፤ ◉"No animal shall kill any other animal" to "No animal shall kill any other animal without cause” ሲሸው እየገደለ
በመጨረሻም አሳማዎቹ (የእንስሳት እርሻ ገዢዎች) በእግራቸው ቆመው መሄድ ጀመሩ (ሁለት እግሬዎች የተሻሉ ናቸው ብለውም ሰበኩ) ፤ በስመዲሞክራሲ ናፓሊዮን ብቻውን ያለበትን ምርጫ ተወዳደረ ፣ በሰው ገበታ ውስኪ ተራጬ ፤ ከሰው ማዕድ ጋ አብረው ቆረሱ "ከሰው እስካይለዩ ድረስ ፤ ከሰው ተመሳሰሉ " ልዕለ ሕግም እንዲህ አወጡ፦ “ALL ANIMALS ARE EQUAL BUT SOME ANIMALS ARE MORE EQUAL THAN OTHERS”.
_
ሩሲያዊያንም የተጋደሉለት አብዮት ከሰመ ፤ ስታሊንም ካወቋቸው መሪዎች ሁሉ ፍርደገምደልና ጨካኝ ነበር ፤ ከአንደኛው ንግግሩ እንዲህ አለ “Death solves all problems - no man, no problem.” _ BINIYAM T.
⁵principles of uncertainty ⁶Georg Carlin ⁷Rules of recognition