January 9, 2025

ቃል ማለት

ዮሐንስ ፬ vs 10 - 11 ኢየሱስም፣ “የእግዚአብሔርን ስጦታ ብታውቂና ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑን ብትረጂ ኖሮ፣ አንቺው በጠየቅሽው፣ እርሱም የሕይወትን ውሃ በሰጠሽ ነበር” ሲል መለሰላት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ከዚህ ውሃ የሚጠጣ እንደ ገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል።”

thumbnail
avatar

Biniyam

Poetry

Vivid Voices | Biniyam T.

ጋላሞታይቱ 
የየሰርጣሰርጧን 
በደል እያሰላች

ሀጥያተ : አምሳሏ የሰለለ : ድምጿን እየሞዣዠረች

ቀና : ብላ : ድንገት
ኢየሱስ : ክርስቶስን
ግርምቷን : ጠየቀች

አይሁድ : ሆነህ : እንዴት ?

እኔ : የማውቀው : አይሁድ ከዚያ : ማዶ : መንደር የተሰነደረ

የጎደፈ : ነፍሴን
የፀለመ : እውኔን
እጅ : እየቀሰረ 

ስናድር : አንግቶ
ሰናፍሉን : ታጥቆ
ይጀነን : ነበረ  

አይሁድ : ሆነህ : እንዴት ?

ባታውቀው : ነው 'ጂ
የእይታ : ደርዟ
ከአድማስ : ባይሻገር 

አጠገቧ : ሆኖ
ውሃ : የሚጠይቃት

የእግዚአብሔር ፡ ቃል : ነበር

ቃል : ማለት : ድልድይ : ነው ፤

በእምነት : ከፍታ
በማስተዋል : ድርሳን
ከአብ : ያስታረቀ

' ቃልነት ' : ትንፋሽ : ነው !

የቆሸሸ : ነፍሴን
በደም : አፀዳድቶ
ህይወት : ያረቀቀ 

ቃል : ማለት : እውነት : ነው !

ሰማይ : ዘረጋግቶ
መሬት : አነጣጥፎ
በ ' ሁን ' ያፀደቀ

ብስረተ ሰማያት

ሰመመናም : መንገድ
መንገድ : መዳረሻ
የሚያሰናክላት

ስሟ : ለጎደፈ
በስሙ : እንዲሰይማት

የሕይወት : ውሃ : ሰጣት

.

.

ስሟን : ስሰይማት ፦

በጠራራ : ፀሐይ
እንስራዋን : ትታ

ቀትር : 6 : ሰዓት
ያስበረገጋትን
የሰርክ : ጥሟን : ረስታ

ታውደለድላለች

.

.

ምንድን ነው? ስትባል

.

.

ሞጋቿ : ክርስቶስ

ዘለዓለም : ሊያረካት

ያፈለቀውን : ወንዝ

ልቧን : ታሳያለች